በሰሜን ጎንደር በቋራ ሽንፋና አካባቢ አመፁ አገርሽቷል ::

በሰሜን ጎንደር በቋራ ሽንፋና አካባቢው ከዚህ በፊት ወያኔ በለኮሰው የአማራን እና ቅማንት ማህበርሰብ ላይ ለማጋጨት በፈፀመው ሴራ ላይ ለማክሸፍ ህዝብን ያረጋጉ እና ያሰባስቡ በነበሩ ግለሰብፕች ላይ አፈሳ እና እስራት ማድረጉ ይታወቃል ከነዚህም ሰለባዎች መካከል
1- መ/ አለቃ ደጀኔ ወርቁ
2- አቶ አታላይ ደምሴ
3- አቶ ጋሹ ጌጡ
4- አቶ ነጋ ጌጡ
5- አቶ አስቻለው እና ሌሎች

በርካታ እስረኞችን ለ2 ወር ካለምንም ፍርድቤት ክስ ታስረው ሚሰቃዩትን ሰዎችን ትላንት በቀን 19/07/ 2008ዓ፡ም ህውሀት ወያኔ ከተላላኪው በአዴን ተቀብሎ ከሽንፋ ፖሊስ ጣቢያ አውጥቶ ሊወስዳቸው ሲል በህዝቡ ንቁ ተሳትፎ ጥቆማ የሽንፋ ህዝብ ተኩስ በመክፈት ከወያኔ አፈና በማስቀረት ፖሊስ ጣቢያው በህዝብ ተከቦ አድሯል፡፡ ሁሉም የህዝብ ተቃማት ት/ ቤቶች ፥ ባንክ እና የግል ድርጅቶች ከትላንት ከቀኑ 6፥00 ሰዓት ጀምሮ ተዘግተዋል ሁሉም እንቅስቃሴዎች ቁመዋል ህዝብ እና ወያኔ ተፋጠዋል፡፡

 

Source: Mereja.com

Add your comment

Your email address will not be published.