የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርእይ ከግንቦት 17 – 22 ቀን በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲካሔድ ዕውቅና አገኘ

  • የአዲስ አበባ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ዕውቅናውን የሰጠው፥ ዛሬ፣ ሚያዝያ 11 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ ከጠዋቱ 3፡00 ላይ እንደኾነ የማሳወቂያ ቅጹ ያመለክታል፡፡
  • “የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ማሳወቅ” በሚል ዓላማ ከግንቦት 17 – 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሸት 4፡00 ድረስ ለሚካሔደውና ከ100 ሺሕ በላይ ተመልካች እንደሚጎበኘው ለሚጠበቀው ዐውደ ርእይመንግሥት የፖሊስ ጥበቃ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
  • የማኅበሩ አመራርና የዝግጅቱ ዐቢይ ኮሚቴ፣ ቀደም ሲል ከመጋቢት 15 እስከ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በዚያው በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲካሔድ ታቅዶ የነበረው የ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ መርሐ ግብር ባልተለመደ ሕግና አሠራር እክል ከገጠመው ደቂቃ ጀምሮ፥የአዲስ አበባ አስተዳደርንና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጨምሮ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ ሓላፊዎች ጋር ተደጋጋሚና እልክ አስጨራሽ ውይይቶችን በትዕግሥት ሲያካሒድ ሰንብቷል፡፡

 

Hara Tewahido

Add your comment

Your email address will not be published.

1 Comment

  • Rago Birru 9 years ago

    Is the dispute between ማቅ and Synods resolved? If yes, nice to hear this status update. If no, how do I go to the exhibition having discomfort please?

    Reply